Featured In

Lyrics

ምነው በጾም በጸሎት ሲሻው ሀገር
ገፋሽ ፍቅርን የሚያህል ንፁህ ነገር
ተይ ተይ የነገው ቤትሽ ቢታደስም
አይበጅ ረግጦ ሰው መሄድ የት ሊያደርስ
ምነው በጾም በጸሎት ሲሻው ሀገር
ገፋሽ ፍቅርን የሚያህል ንፁህ ነገር
ተይ ተይ የነገው ቤትሽ ቢታደስም
አይበጅ ረግጦ ሰው መሄድ የት ሊያደርስ
አንድ ቀን እንደማጣሽ ምን ነበር በሳልኩት
መሄድም ባልከፋኝ ልቤን ባሳመንኩት
ክህደትሽ አሳልፎ ለሀዘን ከሰጠኝ
ለኔስ ይሁዳ ነሽ ሌላ ቃልም የለኝ
እንኳን ቀረ በዚሁ ደ'ሞ ለሌላ ሀጥያት
ከምትሰጫት ለበቀል የልቤን ከረጢት
ያመነን እየሳሙ ለጥቅም ቢሸጡት
ገንዘቡ አኬልዳማ ትርፉ የደም መሬት
መርጬሽ ከሰው ስልጣን ብሰጥሽ ከልቤ ጓዳ
አንቺ ለወጥሺኝ በማይሆን ነገር እንደ ይሁዳ
መርጬሽ ከሰው ስልጣን ብሰጥሽ ከልቤ ጓዳ
አንቺ ለወጥሺኝ በማይሆን ነገር እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ (ዋይ ዋይ)
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ (ዋይ ዋይ)
እንደ ይሁዳ
ምነው በጾም በጸሎት ሲሻው ሀገር
ገፋሽ ፍቅርን የሚያህል ንፁህ ነገር
ተይ ተይ የነገው ቤትሽ ቢታደስም
አይበጅ ረግጦ ሰው መሄድ የት ሊያደርስ
ምነው በጾም በጸሎት ሲሻው ሀገር
ገፋሽ ፍቅርን የሚያህል ንፁህ ነገር
ተይ ተይ የነገው ቤትሽ ቢታደስም
አይበጅ ረግጦ ሰው መሄድ የት ሊያደርስ
አምላኬን እንዳልለው የእምነቴን ዋልታ
ስራዋን እሷ አታውቅም ይቅር በላት ጌታ
በፍቅር እያመኑ በዘላለም ጉልበት
ሰው እንዴት ይሄዳል ምንም ሳይጎልበት
አመል ሆኖብሽ እንጂ በቤት ንብረት ደጃፌ
አንቺ ነበርሽ አዛዡ በጓዳው ሳታኮርፊ
እንኳን ተበዳይ ሆነው ጥቅም ሳያውካቸው
ለፍቅር ሲሉ 'ሚያልፉ በርግጥ ብፁዓን ናቸው
የማዝነው ላንቺ ሄደሽ ለሸመትሽ የህሊና እዳ
ያጎረሰሽን እጄን ለነከስሽ እንደ ይሁዳ
የማዝነው ላንቺ ሄደሽ ለሸመትሽ የህሊና እዳ
ያጎረሰሽን እጄን ለነከስሽ እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ (ዋይ ዋይ)
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ (ዋይ ዋይ)
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ (ዋይ ዋይ)
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ
እንደ ይሁዳ (ዋይ ዋይ)
እንደ ይሁዳ
instagramSharePathic_arrow_out