Top Songs By Ephrem Tamiru
Similar Songs
Credits
PERFORMING ARTISTS
Ephrem Tamiru
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Yilma G/Ab
Songwriter
Elias Woldemariam
Songwriter
Lyrics
ተጠቧል አምላክ ባንቺ ላይ
ሲሰራሽ ከሌሎች በላይ
ልቅም አድርጎ የፈጠረሽ
እንከን የሌለሽ ቆንጆ ልጅ ነሽ
ተጠቧል አምላክ ባንቺ ላይ
ሲሰራሽ ከሌሎች በላይ
ልቅም አድርጎ የፈጠረሽ
እንከን የሌለሽ ቆንጆ ልጅ ነሽ
ዜማ ቢፃፍልሽ ቢገጠም ስላንቺ
ለድርሰቱ ማማር አቤት ስትመቺ
ቁመና መልክሽ ደራሲ ያሻዋል
ሃገሩን ሁሉ ሙሉ አርገሺዋል
ቅኔ ቢቀኙልሽ እያሞጋገሱ
ማህሌት ያስቆማል ተፈጥሮሽ
ታጣልሽ ወገን ምትክ አምሳያ
ሆነሽ ተፈጥረሽ ታምር ማሳያ
ተገርሞ ተደንቆ እያየሽ
በውበት በቅርፅሽ
ብዙ ሰው ይፈዛል በመልክሽ
ልዩ ናት እያለሽ
አልተገኝም ልክሽ ልክሽ
ዕድል ስጪኝ ላውራሽ እባክሽን
እባክሽ
እባክሽ
እባክሽ
ተጠቧል አምላክ ባንቺ ላይ
ሲሰራሽ ከሌሎች በላይ
ልቅም አድርጎ የፈጠረሽ
እንከን የሌለሽ ቆንጆ ልጅ ነሽ
ተጠቧል አምላክ ባንቺ ላይ
ሲሰራሽ ከሌሎች በላይ
ልቅም አድርጎ የፈጠረሽ
እንከን የሌለሽ ቆንጆ ልጅ ነሽ
በገና ለያሬድ መሰንቆንም ለዛር
መልክን ላንቺ ሰጠ አቤት ያምላክ ስራ
ከየት ልነሳ ከምን ልጀምር
ከፀጉርሽ እስከግርሽ ቁመናሽ ሲያምር
የቁንጅና ሚዛን እናርግሽ መለኪያ
ማን ይቁም በቦታው የለሽም መተኪያ
ለናሙና እንኳን ቢፈለግ በዐለም
በዚ ምድር ላይ አምሳያሽ የለም
ደጉ አምላክ ዘመኑን ያንቺ አርጎት
አድሎሽ ማማሩን
ቢሰራሽ አስመኘኝ በቁንጅናሽ
ካንቺ ጋር መኖርን
አልተገኝም ልክሽ ልክሽ
ዕድል ስጪኝ ላውራሽ እባክሽን
እባክሽ
እባክሽ
እባክሽ
Written by: Elias Woldemariam, Yilma G/Ab