Lyrics
ኦሆ ኦሆ ኦሆ
እቤት ካሉት ይልቅ
የጠፉት በጎቿን
ኢትዮጵያም እንደ አምላክ
ናፍቃለች ልጆቿን
አዬይ አሆ
ወሰወሰው ልቤን ወሰወሰው
ሁለት ፍቅር ይዞኝ አንድ ሰው
ወሰወሰው ልቤን ወሰወሰው
አንድም ከሃገር
አንድም ከሃገሬ ሰው ወሰወሰው
ነህ ወይ ነህ ወይ
ናፍቆት እሳት ነህ ወይ
ነህ ወይ ነህ ወይ
ናፍቆት ነፋስ ነህ ወይ
ነህ ወይ ነህ ወይ
ብንን ብንን ተው አታድርገኝ
ሃገር እንደሌለኝ አታቅልለኝ
እማሆይ እማሆይ እማሆይ
ጸሎትሽ ተሰማልሽ ወይ?
እማሆይ እማሆይ እማሆይ
ስለትሽ ሠመረልሽ ወይ?
ኦሆሆሆሆሆሆ
የማይቻል የለም (ኑ ኑ)
ፍጹም ላንተ ጌታ (ኑ ኑ)
ሰብስበህ አኑረን (ኑ ኑ)
የፈጠርከን ቦታ (ኑ ኑ)
እንደ ሰው በባህር (ኑ ኑ)
እንደ ዓሳ በምድር (ኑ ኑ)
ሆነን እንዳንቀር (ኑ ኑ)
አምላክ ስጠን ፍቅር (ኑ ኑ)
አፈሩን ከመናፈቅ በቀር
ምን እረፍት ይኖራል ሰው ሃገር
ሲከፋው አይቶ ብዙ ነገር
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ችግሯን ጉዳቷን እይላት
ናፍቆቷን ጥሟን ቁረጥላት
ልጆቿን ሰብስበህ አምጣላት
ሃገሬ (ትደሰት የኔ እናት)
ኢትዮጵያ (ትደሰት የኛ እናት)
ሃገሬ (ትደሰት የኔ እናት)
ኢትዮጵያ (ትደሰት የኛ እናት)
ሃገሬ (ትደሰት የኔ እናት)
ኢትዮጵያ (ትደሰት የኛ እናት)
ከድህነቷ ላይ ቆርሳ
ያሳደገችን አድርሳ
እማማ ኑ ኑ ትላለች
ውጪ ውጪውን እያየች
ሃገሬ ኑ ኑ ትላለች
ልጆቿን ትናፍቃለች
ኑ ኑ ኑ ኑ ኑ
ኑ ኑ ኑ ኑ ኑ
ኑ ኑ ኑ ኑ ኑ
ኑ ኑ ኑ ኑ ኑ
ወሰወሰው ወንዝ እያሻገረ
ወሰወሰው አባይ እንደ አፈሩ
ወሰወሰው ተበታትኖ ቀረ
ወሰወሰው በየሰው ሃገሩ ባላገሩ
ምነው ምነው የሃገሬ ልጅ ምነው
ምነው ምነው የእናቴ ልጅ ምነው
ወገን መሐል ባይበላስ ምነው
ፍቅር ካለ ትንፋሽም ቀለብ ነው
እንጂ ምነው
እማሆይ እማሆይ እማሆይ
ጸሎትሽ ተሰማልሽ ወይ?
እማሆይ እማሆይ እማሆይ
ስለትሽ ደረሰልሽ ወይ?
ኦሆሆሆሆሆሆ
የትም እንዳንቀር (ኑ ኑ)
እድገትን ፍለጋ (ኑ ኑ)
አሳየኝ አምላኬ (ኑ ኑ)
ሃገሬ በልጽጋ (ኑ ኑ)
የተበታተነው (ኑ ኑ)
ሁሉም ተመልሶ (ኑ ኑ)
የምናፍቀው ቀን (ኑ ኑ)
ምነው ባየው ደርሶ (ኑ ኑ)
በደስታ እንዲረዳዱላት
በፀጋ እንዲፋቀሩላት
ሕዝቦቿን ልጆቿን ባርክላት
ሃገሬ (ትደሰት የኔ እናት)
ኢትዮጵያ (ትደሰት የኛ እናት)
ሃገሬ (ትደሰት የኔ እናት)
ተሰድዶ ሄዶ በሰው ሃገር
ጉልበቱን መንዝሮ በማደር
ጨብጦ ያገኛትን ነገር
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
ባላገር (ይላል ሃገር ሃገር)
Written by: Ephrem Tamiru