Music Video

ጊድዮን ዳናኤል ባህር ማዶ Gedion Daniel Bahir Mado lyrics
Watch ጊድዮን ዳናኤል ባህር ማዶ Gedion Daniel Bahir Mado lyrics on YouTube

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Gedion Daniel
Gedion Daniel
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Yilma G/Ab
Yilma G/Ab
Songwriter

Lyrics

ያለሽበት ድረስ እንዳልመጣ ራቀኝ
ተመለሺ ፍቅሬ ብቻዬን ጨነቀኝ
እንዳልመጣ እኔ አቅሜ አልፈቀደልኝ
ድረሺልኝ ነይ ነይ የኔስ ሆድ እምቢ አለኝ
ያለሽው ባሕር ማዶ
ልቤ አለቀልሽ ነዶ
አዬዬ አዬ ነዶ
መጥቼ እንዳላይሽ
አቅሜ እኮ አልፈቀደልሽ
ዋይ ዋይ ዋይ አልፈቀደልሽ
ሰው ኖሮኝ ሰው ያጣሁኝ
ሆኛለሁ ያልታደልኩኝ
አዬዬ ያልታደልኩኝ
ብሶቴን ለማን ልንገር
ጭንቅ ሆኗል የኔስ ነገር
ዋይ ዋይ ዋይ የኔስ ነገር
እንዳልመጣ ርቆኛል
እንደው ምን ይሻለኛል
ብቸኛ አድርጎኛል
ዋይ መላው ጠፍቶብኛል
እንዳልመጣ ርቆኛል
እንደው ምን ይሻለኛል
ብቸኛ አድርጎኛል
ዋይ መላው ጠፍቶብኛል
ላላላላላ...
ላላላላላ...
ያለሽበት ድረስ እንዳልመጣ ራቀኝ
ተመለሺ ፍቅሬ ብቻዬን ጨነቀኝ
እንዳልመጣ እኔ አቅሜ አልፈቀደልኝ
ድረሺልኝ ነይ ነይ የኔስ ሆድ እምቢ አለኝ
ልሂድ ብል ተጓጉዤ
ለስንቅስ ምኔን ይዤ
አዬዬ አዬ ምን ይዤ
እንዳልሄድ አቅም አነሰኝ
ከወዲያ ማን ያድርሰኝ
ዋይ ዋይ ዋይ ማን ያድርሰኝ
ጠቅልዬም እንዳልመጣ
ልብ የለው ገንዘብ ያጣ
አዬዬ አዬ ያጣ
አሰኘኝ እንደ ዋኔ
አቅም ያጣሁ በመሆኔ
ዋይ ዋይ ዋይ በመሆኔ
እንዳልመጣ ርቆኛል
እንደው ምን ይሻለኛል
ብቸኛ አድርጎኛል
ዋይ መላው ጠፍቶብኛል
እንዳልመጣ ርቆኛል
እንደው ምን ይሻለኛል
ብቸኛ አድርጎኛል
ዋይ መላው ጠፍቶብኛል
ላላላላላ...
ላላላላላ...
ላላላላላ...
ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ...
ላላላላላ...
ላላላላላ...
ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ...
ላላላላላ...
Written by: Yilma G/Ab
instagramSharePathic_arrow_out