Music Video

Meselu Fantahun - Wey Limta Wey Mita | ወይ ልምጣ ወይ ምጣ - New Ethiopian Music 2021 - (Official Video)
Watch Meselu Fantahun - Wey Limta Wey Mita | ወይ ልምጣ ወይ ምጣ - New Ethiopian Music 2021 - (Official Video) on YouTube

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Meselu Fantahun
Meselu Fantahun
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Elias Melka Geresu
Elias Melka Geresu
Songwriter

Lyrics

አገሩና ደጄ ሩቅ እየመሰለኝ
እንደ ወፍ እንግዳ እያብሰለሰሉኝ
ዘመድ እንደሌለው እንደ ባዳ አገር ሰው
እንደ ቀልድ ባይተዋር ሆዱን እየባሰው
ወይ ልምጣ ወይ ምጣ
ከሆንክ የኔ እጣ
በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ
አገሩና ደጄ ሩቅ እየመሰለኝ
እንደ ወፍ እንግዳ እያብሰለሰሉኝ
ዘመድ እንደሌለው እንደ ባዳ አገር ሰው
እንደ ቀልድ ባይተዋር ሆዱን እየባሰው
ወይ ልምጣ ወይ ምጣ
ከሆንክ የኔ እጣ
በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ
እጆቼን ዘርግቼ እቀበለው ነበር
የውሃ ሽታ ሆኖ ሄዶ በዛው ባይቀር
በል በርታ በል በርታ ልቤ ጨከን በል
ሲመጣ ይመጣል እውነቱን ተቀበል
ወይ ልምጣ ወይ ምጣ
ከሆንክ የኔ እጣ
በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ
እጆቼን ዘርግቼ እቀበለው ነበር
የውሃ ሽታ ሆኖ ሄዶ በዛው ባይቀር
በል በርታ በል በርታ ልቤ ጨከን በል
ሲመጣ ይመጣል እውነቱን ተቀበል
ወይ ልምጣ ወይ ምጣ
ከሆንክ የኔ እጣ
በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ
እህ እህህህህህህህ
እህ ወየው ጉድ... ስንት አለ በሆዴ
አምቄ ነው እንጂ... ኑሮዬን በዘዴ
አለ ጋደም ጋደም... ሰው ሁሉ ሊተኛ
እኔ ቁጭ ብያለው... ያንተ በሽተኛ
እህ እህህ እህ እህህ
እጆቼን ዘርግቼ እቀበለው ነበር
የውሃ ሽታ ሆኖ ሄዶ በዛው ባይቀር
በል በርታ በል በርታ ልቤ ጨከን በል
ሲመጣ ይመጣል እውነቱን ተቀበል
ወይ ልምጣ ወይ ምጣ
ከሆንክ የኔ እጣ
በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ
ኧረ ያገሬ ልጅ
እናና ዘመዴ
ጉብል ሸጋዬዋ
አሃሃ አሃሃ
እዛም እዛም ያልኩት ሆዳምነቴ ነው
አንጀቴን አስሬ ብጠብቅህ ምነው
ኧረ ያገሬ ልጅ
እናና ዘመዴ
ጉብል ሸጋዬዋ
አሃሃ አሃሃ
ዘመዶቼም ጠሉኝ እኔም ጠላሁዋቸው
ያጣ ሰው አያገኝ እየመስላቸው
እህህ እህህ እህህ እህህ
ወይ ልምጣ ወይ ምጣ
ከሆንክ የኔ እጣ
በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ
ኧረ ያገሬ ልጅ
እናና ዘመዴ
ጉብል ሸጋዬዋ
አሃሃ አሃሃ
ወይ ልምጣ ወይ ምጣ
ከሆንክ የኔ እጣ
በምን ጥፋቴ ነው ልቤ እንዲህ ሚቀጣ
እህህህህህ
Written by: Elias Melka Geresu, Samuel Alemu
instagramSharePathic_arrow_out