Credits
PERFORMING ARTISTS
Bisrat Garedew
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Bisrat Garedew
Songwriter
Lyrics
እኔ አንገቴን ልድፋ ላቀርቅርልሽ
መጨነቅሽ ለምን ነው ስለኔ 'ሚሰማሽ ('ሚሰማሽ)
ምን ባደረግሽ እስኪ ምን በወጣሽ
እኔ አንገቴን ልድፋ ላቀርቅርልሽ
መጨነቅሽ ለምን ነው ስለኔ 'ሚሰማሽ ('ሚሰማሽ)
ምን ባደረግሽ እስኪ ምን በወጣሽ
እኔ እንጂ ለሁሉም ምክንያት መሰረት
እኔ እንጂ ቃሌም የታጠፈ ተጠቂ በወረት
እኔ እንጂ የገዘፈ ሃጥያት የተሸከምኩት
እኔ እንጂ ምን በወጣሽ ብለሽ ማሰብ መፀፀት
እኔ እንጂ ለሃሳብሽ ተቃራኒ ሆኜ
እኔ እንጂ ፍቅሬን የገፋሁት ዓይኔንም ጨፍኜ
እኔ እያለሁ አንገቴንም መድፋት ማቀርቀር ያለብኝ
እኔ እያለሁ ምን በወጣሽ አንቺ አትሳቀቂብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
የዳረግኩሽ ጡርም ያለብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ያልተቀጣሁ ችሎት ያልዳኘኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ፍቅሬንም የገፋሁኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ይሄ የሚገባኝ
እኔ አንገቴን ልድፋ ላቀርቅርልሽ
መጨነቅሽ ለምን ነው ስለኔ 'ሚሰማሽ ('ሚሰማሽ)
ምን ባደረግሽ እስኪ ምን በወጣሽ
እኔ አንገቴን ልድፋ ላቀርቅርልሽ
መጨነቅሽ ለምን ነው ስለኔ 'ሚሰማሽ ('ሚሰማሽ)
ምን ባደረግሽ እስኪ ምን በወጣሽ
እኔ እንጂ የካድኩኝ ሃቅ እውነታውን
እኔ እንጂ ደንዳና ያረኩት ጨካኝ ልቤን
እኔ እንጂ ከላዬ ያልወረደ የህሊና እዳዬ
እኔ እንጂ ማቀርቀር ያለበት ሸክም ያለው ጫንቃዬ
እኔ እንጂ ለሃሳብሽ ተቃራኒ ሆኜ
እኔ እንጂ ፍቅሬን የገፋሁኝ ዓይኔንም ጨፍኜ
እኔ እያለሁ አንገቴንም መድፋት ማቀርቀር ያለብኝ
እኔ እያለሁ ምን በወጣሽ አንቺ አትሳቀቂብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ምን በወጣሽ ምን አጉድለሽብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ለምን ታዝኚ ታቀረቅሪብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ስታመን ያልታመንኩኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ምክንያት የሆንኩኝ
እኔ እንጂ የካድኩኝ ሃቅ እውነታውን
እኔ እንጂ ደንዳና ያረኩት ጨካኝ ልቤን
እኔ እንጂ ከላዬ ያልወረደ የህሊና እዳዬ
እኔ እንጂ ማቀርቀር ያለበት ሸክም ያለው ጫንቃዬ
እኔ እንጂ ለሃሳብሽ ተቃራኒ ሆኜ
እኔ እንጂ ፍቅሬን የገፋሁኝ ዓይኔንም ጨፍኜ
እኔ እያለሁ አንገቴንም መድፋት ማቀርቀር ያለብኝ
እኔ እያለሁ ምን በወጣሽ አንቺ አትሳቀቂብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
የዳረግኩሽ ጡርም ያለብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ያልተቀጣሁ ችሎት ያልዳኘኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ፍቅሬንም የገፋሁኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ይሄ የሚገባኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ምን በወጣሽ ምን አጉድለሽብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ለምን ታዝኚ ታቀረቅሪብኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ስታመን ያልታመንኩኝ
እኔ ነኝ እኔ ነኝ
ምክንያት የሆንኩኝ
Written by: Bisrat Garedew