Music Video

Mikias Chernet Ahun Gebagn Lyrics ሚኪያስ ቸርነት አሁን ገባኝ lyrics
Watch Mikias Chernet Ahun Gebagn Lyrics ሚኪያስ ቸርነት አሁን ገባኝ lyrics on YouTube

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Mikyas Cherinet
Mikyas Cherinet
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Mikyas Cherinet
Mikyas Cherinet
Songwriter

Lyrics

እቴ ልማልልሽ እቴ ልማልልሽ እኔ ልማል
አስቀይሜሻለሁ ጥፋቴ ገብቶኛል ፀፅቶኛል
ሆዴ ልማልልሽ እኔ ልማልልሽ እኔ ልማል
አስቀይሜሻለሁ ህመምሽ አሞኛል ተሰምቶኛል
መቼም አውቃለሁ ሃዘን ትካዜው አይገባኝም አልልም ደርሶ
የጁን ያገኛል ሰው የዘራውን ያጭዳል መልሶ
አጕጉል አርጋኝ አሰነካክላኝ ሄዳለሽ ብዬ አልኮንንሽም
ብዙ ሞክረሽ ችለሽኝ ነበር አልሆንልሽም
ካጣሁሽ ወድያ ፊቴን ብቧጥጥ ጥፍሬን ብበላው
ትርፉ ህመም ነው መልሶ አይመጣም መቼም የኋላው
ሊሆን የማይችል ድንገት ይሆናል ድንገት ይሆናል
ጨበጥኩት ያሉት ከጉም ይበናል ከጉም ይበናል
የገባኝ እንዳልገባኝ እንዳልገባኝ
ያልገባኝ እንደገባኝ ገና አሁን ገባኝ
እንዳልጠግነው ሰዓቱ ረፍዷል
ሰዓቱ ረፍዷል
የሆነው ሁሉ እንዳይሆን ሆኗል
እንዳይሆን ሆኗል
የገባኝ እንዳልገባኝ እንዳልገባኝ
ያልገባኝ እንደገባኝ አሁን ገባኝ
ፀፀት ሸከፎ ሌቱ እንደነጋው ቀኑም ይመሻል
ልደበቅ ቢልስ ሰው ከህሊናው ወዴት ይሸሻል
ወዴት ይሸሻል
ወዴት ይሸሻል
ወዴት ይሸሻል
እቴ ልማልልሽ እቴ ልማልልሽ እኔ ልማል
አስቀይመሻለው ጥፋቴ ገብቶኛል ፀፅቶኛል
ሆዴ ልማልልሽ እኔ ልማልልሽ እኔ ልማል
አስቀይሜሻለሁ ህመምሽ አሞኛል ተሰምቶኛል
አንዴ የበተኑት ከሆነ ወድያ እንደነበረው ላይሰበሰብ
አውቆ ገምቶ ቀድሞ ነበረ እንጅ መጭውን ማሰብ
ዛሬ ደፍሬ ችዬ ባልልም እንደበፊቱ አብረን እንሁን
ካለሽበት ዘንድ ይቅርታ አርጊልኝ እራሴን ልሁን
እንኳን ያስብኩት የያዝኩት ጠፋኝ
የያዝኩት ጠፋኝ
የበደል መአበል ወደ ዳር ገፋኝ
ወደ ዳር ገፋኝ
ሃሳብ ከ ጭንቀት እንደው ላይገላግል
ላይገላግል
ጥፋት ብቻ ነው ከራስ ጋር ትግል
ከራስ ጋር ትግል
የገባኝ እንዳልገባኝ እንዳልገባኝ
ያልገባኝ እንደገባኝ አሁን ገባኝ
እንዳልጠግነው ሰዓቱ ረፍዷል
ሰዓቱ ረፍዷል
የሆነው ሁሉ እንዳይሆን ሆኗል
እንዳይሆን ሆኗል
የገባኝ እንዳልገባኝ እንዳልገባኝ
ያልገባኝ እንደገባኝ አሁን ገባኝ
ፀፀት ሸከፎ ሌቱ እንደነጋው ቀኑም ይመሻል
ልደበቅ ቢልስ ሰው ከህሊናው ወዴት ይሸሻል
ወዴት ይሸሻል
ወዴት ይሸሻል
ወዴት ይሸሻል
Written by: Mikyas Cherinet
instagramSharePathic_arrow_out