歌词

አሰብኩህ ስላየሁ አንዴ በድንገት ወቸው ጉድ ምን ልዩ አረገህ ከፍጥረት ብታምረኝ ተመኘሁህ እና በልቤ ባዋይህ ታድያ ምን አለበት ቀርቤ እንደ ንጋት ጀንበር ፈገግ ያለው ፊትህ ብዙ ኮከቦችን የመሰሉ አይኖችህ አትኩሬ ባያቸው አትኩረው ያዩኛል ፍቅረኛህ እንድሆን አስገድደውኛል ከቆንጆም ቆንጆ አለ ከሸጋም ልጅ ሸጋ ለእኔ አትሰለቸኝም አብረን ብናወጋ አለህ አቀራረብ ያነጋገር ለዛ ሰርጎ ገብን ፍቅር አይለቅ እንደ ዋዛ ቁንጅናህና ደም ግባትህ አትኩሮ ላየህ ልዩ ልጅ ነህ ቁንጅናህና ደም ግባትህ አትኩሮ ላየህ ልዩ ልጅ ነህ ለይስሙላ አይደለም እኔ አንተን ማድነቄ በግልፅ ይታይልኝ ባንተ መደነቄ ካንተጋር በፍቅር ለመኖር ተስፋ አለኝ ብዬ ቃል ገባሁኝ ምን ጊዜም ያንተው ነኝ ከቆንጆም ቆንጆ አለ ከሸጋም ልጅ ሸጋ ለእኔ አትሰለቸኝም አብረን ብናወጋ አለህ አቀራረብ ያነጋገር ለዛ ሰርጎ ገብን ፍቅር አይለቅ እንደዋዛ ቁንጅናህና ደም ግባትህ አትኩሮ ላየህ ልዩ ልጅ ነህ ቁንጅናህና ደም ግባትህ አትኩሮ ላየህ ልዩ ልጅ ነህ ቁንጅናህና ደም ግባትህ አትኩሮ ላየህ ልዩ ልጅ ነህ ቁንጅናህና ደም ግባትህ አትኩሮ ላየህ ልዩ ልጅ ነህ
Writer(s): Elias Woldemariam, Tesfaye Abebe Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out