Music Video

Teddy Afro - Helm Aydegemem (Lyrics) | Ethiopian Music
Watch Teddy Afro - Helm Aydegemem (Lyrics) | Ethiopian Music on YouTube

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Teddy Afro
Teddy Afro
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Teddy Afro
Teddy Afro
Songwriter

Lyrics

ህልም አይቼ ማታ ከማዶ መስኩ ላይ ቁጭ ብለን ዋርካዉ ስር ፍቅርን ስንወያይ የሚወድሽ ልቤ ገና አይቶሽ ሳይበቃዉ በእጆችሽ ደባብሰሽ ልታቅፊኝ ስል ነቃው ምናለ ባልነቃስ ከእንቅልፌ እንዳድር በክንድሽ ታቅፌ ብተኛ ተመልሼ እንዳልም ለካ አንዴ ነዉ ህልም አይደገምም የቤቴ ጓዳ አልጋ አንሶላዉ ትራሴ አሳፍሮኝ ካንችዉ ዘንድ ደስ ሲላት ነፍሴ ጎኔን ላመቻቸዉ ስገላበጥ ነቃው የሚወድሽ ልቤ አልሞሽ ሳይበቃዉ አዬ ድንገት ነቃሁ የናፍቆቴን ረሃብ ካልጠገብኩሽ ስሜ አይፈታም እና የሌሊቱ ህልሜ ሳልም የእዉነቴን ነዉ እኔ አላዉቅም ዉሸት ተይ መጥተሽ ደባብሽኝ ህልሜ እንዳይሆን ቅዠት ኦሆይ ኦሆሆኦሆይ አሃ አሃሃሃአሃይ አሃ አሃሃሃአሃይ ህልም አይቼ ማታ ከማዶ መስኩ ላይ ቁጭ ብለን ዋርካዉ ስር ፍቅርን ስንወያይ የሚወድሽ ልቤ ገና አይቶሽ ሳይበቃዉ በእጆችሽ ደባብሰሽ ልታቅፊኝ ስል ነቃው ምናለ ባልነቃስ ከእንቅልፌ እንዳድር በክንድሽ ታቅፌ ብተኛ ተመልሼ እንዳልም ለካ አንዴ ነዉ ህልም አይደገምም ጭር ባለዉ ሌሊት ጨለማዉን ጥሶ ይመለሳል ልቤ ካለሽበት ደርሶ ቢርቅም ቅርብ ነዉ ያለሽበት ቦታ ተኝቼ ሳልምሽ ምን ተሰማሽ ማታ አዬ ባክሽ ማታ ወፎች ሳይንጫጩ ሳሩ ሳይዝ ጤዛ ተገኘሁ በህልሜ እዚህ ተኝቼ እዛ ባሸለበዉ ሰማይ ስትናፍቂያት ነፍሴን ወዳንቺ የሚያመጣኝ ህልም ነዉ ፈረሴ ኦሆይ ኦሆሆኦሆይ አሃ አሃሃሃአሃይ ኦሆይ ኦሆሆኦሆይ አሃ አሃሃሃአሃይ
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out