Top Songs By Abeba Desalenge
Credits
PERFORMING ARTISTS
Abeba Desalenge
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Temesgen Afework
Songwriter
Lyrics
ድምሬ በሆንክልኝ ደስታዬ በሞላልኝ
ስጦታ በሆንኩለት በእቅፉ በዋልኩለት
የትኛዉ ተራራ ሸስጎህ ነበረ
ባላመንኩት ቦታ ልቤ ከታሰረ
እንባ ሞልቶት አይኔን ከልሎኝ የፊቴን
አንተን መሳይ ጉብል ነፈኩት ህይወቴን
ዘመን ተመልሶ በእቅፍህ በዋልኩኝ
ከፍቅርህ ሁዳዴ በአንተዉ በገደፍኩኝ
የፍቅር ቡቃያ ጭንጫ ላይ ዘርቼ
ስንት ዘመን ገብቶ የአንተን ብጤ አጥቼ
የት ነበርክ ልበልህ በከፋዉ ዘመኔ
እንኳንስ ገላዬ ሲናፍቅህ አይኔ
ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን
ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን
ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
ድምሬ በሆንክልኝ ደስታዬ በሞላልኝ
ስጦታ በሆንኩለት በእቅፉ በዋልኩለት
የትኛዉ ተራራ ሸስጎህ ነበረ
ባላመንኩት ቦታ ልቤ ከታሰረ
እንባ ሞልቶት አይኔን ከልሎኝ የፊቴን
አንተን መሳይ ጉብል ነፈኩት ህይወቴን
ዘመን ተመልሶ በእቅፍህ በዋልኩኝ
ከፍቅርህ ሁዳዴ በአንተዉ በገደፍኩኝ
አሻግሬ ሳየዉ ዘመኔ ይቆጨኛል
ለአንተ አለመዋሉ ያንገበግበኛል
በቃ እንግዲህ ሳልሆነዉ ክፉ ደግ አይቼ
አንተን ሰፈርኩበት ከሌሎች ለይቼ
ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን
ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን
ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
የማይሰማ ምጣድ ሳስስ ፣ የፈሰሰ ዉሃ ሳፍስ
ፈጀሁት ዘመኔን አንድጄ ፣ የማይበስል እንጐቻ ጥጄ
የማይሰማ ምጣድ ሳስስ ፣ የፈሰሰ ዉሃ ሳፍስ
ፈጀሁት ዘመኔን አንድጄ ፣ የማይበስል እንጐቻ ጥጄ
ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን
ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን
ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን
ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
ለአይኔ ነበርክ የኔ ሳይሆን
ቀረ ወይኔ ይቅር ያ ዘመኔ
Writer(s): Elias Woldemariam, Temesgen Afework
Lyrics powered by www.musixmatch.com