Top Songs By Bezuayehu Demissie
Similar Songs
Lyrics
ፍቅሯ ቀለለ ስል እሷን አዘዘብኝ
ልታንገላታኝ ነው ወይ እዳዬ
እሺም አልል እምቢ
እንደፈቀደችው ትዘዝ በገላዬ
ወይ ዕዳዬ አበሳዬ
ወይ ዕዳዬ አበሳዬ
ፍቅሯ ቀለለ ስል እሷን አዘዘብኝ
ልታንገላታኝ ነው ወይ ዕዳዬ
እሺም አልል እምቢ
እንደፈቀደችው ትዘዝ በገላዬ
ወይ ዕዳዬ አበሳዬ
ወይ ዕዳዬ አበሳዬ
ለጠየቅኩት ምላሽ ለወሬው ጣዕምና
መስጠት ጀምሬያለሁ አይደለሁ እንዳምና
ዘንድሮስ ደህና ነኝ በጣም ተሽሎኛል
እያልኩኝ ሳወራ ለካ ፍቅር ይዞኛል
አገኘው እፎይታ ብዬ ተዝናንቼ
የፍቅር ዕዳ አለብኝ ሳልከፍለው ዘንግቼ
ያለብኝን እዳ እሷው ፈረደችው
በናፍቆቷ ወጥመድ አስራ አቀለለችው
ፍቅሯ ቀለለ ስል
እሷን አዘዘብኝ ልታንገላታኝ ነው
ወይ እዳዬ
እሺም አልል እምቢ
እንደፈቀደችው ትዘዝ በገላዬ
ወይ ዕዳዬ አበሳዬ
ወይ ዕዳዬ አበሳዬ
መሟገቻ ቋንቋ ቃላት የታጣላት
ዕዳ አበዛችብኝ ሰርቼ 'ማልከፍላት
በገንዘብ አልተምን አልከፍላት ባራጣ
እሺም እምቢም ሳልል በሷ ጉዴ ወጣ
ውበቷን አድናቂ ዝናዋን ለፋፊ
እኔ የሷ ተረች ወዶ ተሸናፊ
ወዘናዬ ሞልቶ ቀለል ሲለው ልቤ
በማልችለው ፍቅር ተሰውሯል ቀልቤ
ፍቅሯ ቀለለ ስል
እሷን አዘዘብኝ ልታንገላታኝ ነው
ወይ እዳዬ
እሺም አልል እምቢ
እንደፈቀደችው ትዘዝ በገላዬ
ወይ ዕዳዬ አበሳዬ
ወይ ዕዳዬ አበሳዬ
ሄዳለች ርቃ እኔስ ብዬ ነበር
ተመልሳ መጣች አወይ የሷ ነገር
ምን ደስታ ቢከበኝ ልቤ አላመለጠም
ወዶ መገበሩን ከሷ አላቋረጠም
ያለየላት ወዳጅ እሷ ወይ የኔ እዳ
አፍርሳ ና አለችው ሰውነቴን ንዳ
የግሌ ሰው መውደድ የኔ ነው የምለው
በሷ ለመታዘዝ ስምምነት አለው
ወይ ዕዳዬ አባሳዬ
እሺም አልል እምቢ እንዳሻት ታድርገኝ
ዕዳዬን ወደድኩት ሁሌም ጎኔ ትገኝ
ተሽጦ አይለወጥ ወይ አይመነዘር
ፍቅርሽን ሀብቴ እያልኩ ከመዘክዘክ በቀር
አልመከር አለ በድፍን መሄዱ
ደግሞ ጀማመረው ልቤ ሰው መውደዱ
አልመከር አለ በድፍን መሄዱ
ደግሞ ጀማመረው ልቤ ሰው መውደዱ
አልመከር አለ በድፍን መሄዱ
ደግሞ ጀማመረው ልቤ ሰው መውደዱ