Music Video

Tsedenya G/Markos - Himemie New clip New single
Watch Tsedenya G/Markos - Himemie New clip New single on YouTube

Featured In

Top Songs By Tsedenya G

Credits

PERFORMING ARTISTS
Tsedenya G
Tsedenya G
Performer
Markos
Markos
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Abiel Pawolose
Abiel Pawolose
Arranger
MATI
MATI
Arranger
Teremage Woretaw
Teremage Woretaw
Arranger

Lyrics

እጅህ ይዳብሰኝ ዞሮ ከወገቤ
ይወገዳል ጭንቄ ይርቃል ሀሳቤ
ልበልህ ሀኪሜ ልበልህ ፈዋሼ
ሰላም የሰጠኸኝ ጤናዬ ዳባሼ
የተባረከ እጅ በአምላክ የተቀባ
ቢታቀፉት ፍቅር ቢያሸቱት አበባ
ያምላክ ቅበዓቅዱስ የቸርነት ጥበብ
በእጅም ይገለፃል በሰው በሰበብ
ነካካው ገላዬን አካሌን ደባብሰው
በመዳፍህ አይደል የልብ የሚደርሰው
ታከምኩኝ በጆችህ ሆንኩኝ በመዳፍህ
ራኩኝ ከህመሜ በገላህ በእቅፍህ
ማነው ያስተማረህ እንዲህ ያለ ጥበብ
በእጅ እየነኩ በጤና መሰብሰብ
በሀኪም በፀበል መላ የጠፋለት
በእጆችህ መዳፍ ዳንኩኝ እንደዘበት
ህመሜ ህመሜ ህመሜ ህመሜ
ህመሜ ህመሜ ህመሜ ህመሜ
ህመሜ ህመሜ ህመሜ ህመሜ
ህመሜ ህመሜ ህመሜ ህመሜ
እንደ ጀንበር ሞቅኩት እጁን እንደ ፀሀይ
የመዳፉን ብርሃን ለማንም ሳላሳይ
አልተክል አበባ ቤቴን እንዲያደምቀው
እጁ ይበቃኛል መአዛ እሚያፈልቀው
ሐርና ሱፍ ሆነኝ እጅና መዳፉ
ነፍሴን እያሞቃት ሰብስቦ ከእቅፉ
አንድም ተፈወስኩኝ አንድም ተደገፍኩኝ
በእጁ በመዳፉ ስንቱን ተሻገርኩኝ
እንዳማረ ሸማ እንዳማረ ፈትል
ይደምቃል ገላዬ ከሱ ጋራ ስውል
ማን አለ በምድር እንደኔ የረታ
በወዳጁ መዳፍ ህልሙ የተፈታ
ህመሜን በክንዱ ህመሜን በእቅፉ
ህመሜን በክንዱ ህመሜን በእቅፉ
ህመሜን በክንዱ ህመሜን በእቅፉ
ህመሜን በክንዱ ህመሜን በእቅፉ
instagramSharePathic_arrow_out