Music Video

Ethiopian Music Abdu Kiar - Ayzoh 2024 አብዱ ኪያር - አይዞህ
Watch Ethiopian Music Abdu Kiar - Ayzoh 2024 አብዱ ኪያር - አይዞህ on YouTube

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Abdu Kiar
Abdu Kiar
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Abdu Kiar Kahssay
Abdu Kiar Kahssay
Songwriter

Lyrics

ወደቅኩኝ አትበል ምንድነው መውደቅ
ተነሳ እንደገና ደጋግመህ ዉደቅ
ዛሬ ላይ ነው እንጂ የሚጨንቅህ
እመነኝ ነገማ ድል አለልህ
አይችልም ይሉሃል ያጣጥሉሃል
ሞራልህን ሰብረው ታች ይጥሉሃል
ጠንክረህ በርትተህ ስታሳያቸው
ሰማይ ይሰቅሉሃል ሰላም በላቸው
አንተ ልዩ ሰው አይዞህ አንተ የኔ ጀግና አይዞህ
ዛሬን እለፈው አይዞህ በርታ በልና አይዞህ
መውደቅ መሸነፍ አይዞህ ያለነውና አይዞህ
አልፈህ አሳየኝ አይዞህ ይሄን ፈተና አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
ይቺ አለም እንደዚ ናት አለም እንዲ ናት
ይቺ አለም እንደዚ ናት አለም እንዲ ናት
ጎብዘህም ይከብዳል አለም እንዲ ናት
እንኳንስ ሰንፈህላት አለም እንዲ ናት
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
ይቺ አለም እንደዚ ናት አለም እንዲ ናት
ይቺ አለም እንደዚ ናት አለም እንዲ ናት
ጠንክረህም አትሞላም አለም እንዲ ናት
ዘላለም ጎዶሎ ናት አለም እንዲ ናት
ትላንት ያልተሳካው ለምንድነው በል
ስህተትህን እወቅ አምነህ ተቀበል
ዛሬ ላይ ስህተቱን አርመህ ሞክር
ምክንያት አታብዛ ሰበብ አትደርድር
ወደቅኩኝ ያልክ ቀን ያኔ ይጥሉሃል
ሞቻለሁ ያልክ ቀን ያኔ ይገሉሃል
ጠንክረህ በርትተህ ስታሳያቸው
ያኔ ይከተሉሃል እንደዚህ ናቸው
አንተ ልዩ ሰው አይዞህ አንተ የኔ ጀግና አይዞህ
ዛሬን እለፈው አይዞህ በርታ በልና አይዞህ
መውደቅ መሸነፍ አይዞህ ያለነውና አይዞህ
አልፈህ አሳየኝ አይዞህ ይሄን ፈተና አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
ይቺ አለም እንደዚ ናት አለም እንዲ ናት
ይቺ አለም እንደዚ ናት አለም እንዲ ናት
ጎብዘህም ይከብዳል አለም እንዲ ናት
እንኳንስ ሰንፈህላት አለም እንዲ ናት
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
ይቺ አለም እንደዚ ናት አለም እንዲ ናት
ይቺ አለም እንደዚ ናት አለም እንዲ ናት
ጠንክረህም አትሞላም አለም እንዲ ናት
ዘላለም ጎዶሎ ናት አለም እንዲ ናት
ያኔ በልጅነት በዳዴው ዘመን
አንድ እርምጃ መሄድ ነበር ማይታመን
እመን እመን ሲልህ በራስህ እመን
ልብህን ሰማኸው በመተማመን
ወድቆ መነሳትን ተለማመድከው
እግርህን አፀናህ ተረማመድከው
ዛሬም እንደዚህ ነው በራስ ህ እመን
አዸርገዋለሁ በል በመተማመን
አንተ ልዩ ሰው አይዞህ አንተ የኔ ጀግና አይዞህ
ዛሬን እለፈው አይዞህ በርታ በልና አይዞህ
መውደቅ መሸነፍ አይዞህ ያለነውና አይዞህ
አልፈህ አሳየኝ አይዞህ ይሄን ፈተና አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ
Written by: Abdu Kiar Kahssay
instagramSharePathic_arrow_out