Music Video

Mikael belayneh 'ሚካኤል በላይነህ' liwedat nw mesel 'ልወዳት ነው መሰል' lyrics by Ethiolyrics
Watch Mikael belayneh 'ሚካኤል በላይነህ' liwedat nw mesel 'ልወዳት ነው መሰል' lyrics by Ethiolyrics on YouTube

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Michael Belayneh
Michael Belayneh
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Michael Belayneh Hailu
Michael Belayneh Hailu
Songwriter
PRODUCTION & ENGINEERING
Michael Belayneh
Michael Belayneh
Producer

Lyrics

ይመጣል ናፍቆቷ ላያስተኛኝ ምሎ
የልቤን መሳነፍ መራቅ ተከትሎ
ደጋግሞ ከአይኔ ላይ ምስሏ ይከሰታል
አብዝቼ ያሰብኩት ሰው እንደሷ የታል
ተናውጣለች ነፍሴ በእንግዳ ማእበል
ግን ሳለየው እንዴት አፈቀርኳት ልበል
በትር እንደቃጣች አልመክት በክንዴ
ለዛ ልብ ታጋይ ልረታ ነው እንዴ
ተፈጥራ እንጂ ይውደድሽ ተብላ
ስሜቴን ምን ለየው ከሌላ ከሌላ
መላመድ አልለው ገና በሳምንቱ
አይኖቿን መናፈቅ ምንድነው ምክንያቱ
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል በቃል ያወደስኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል በአይኔ የናፈኩት
ይመጣል ናፍቆቷ ላያስተኛኝ ምሎ
የልቤን መሳነፍ መራቅ ተከትሎ
ደጋግሞ ከአይኔ ላይ ምስሏ ይከሰታል
አብዝቼ ያሰብኩት ሰው እንደሷ የታል
ጉልበት ሰቷት እንጂ ልቤ እሷን ማለቱ
ምን ያቆነጃታል ታድያ በየለቱ
ልወዳት ካልሆነ ፍቅሯ ሊቆራኘኝ
እሷን ብቻ ሚያሰኝ ምን ነገር አገኘኝ
ናፍቄ አልጠግብ ያቺን አደይ መሳይ
ደስ ይለኛል ደሞ ተገኝታ አይኖቿን ሳይ
ስሰነብት ሌት ቀን ሲቆጠር
ፍቅሯ ክንፍ አርጎኝ መታየቴ አይቀር
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል ሳላውቅ ያመንኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል ሁሌ ያስታወስኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል በቃል ያወደስኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል በአይኔ የናፈኩት
Written by: Michael Belayneh Hailu
instagramSharePathic_arrow_out