Letra

የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ የሦስት ሺህ ዓመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ እቴ አንቺ የኔ ሙሽራ ሃገሬ እስኪ ልጠይቅሽ ያገቡሻል ይፈቱሻል ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ ከክብርሽ በታች ወደቁ ነገሥታት በፍቅርሽ ተነድፈው ደናግላን መነኑልሽ ዓለምን ደስታቸውን ጥለው እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም (እማማ እማማ) ዘመን አመጣሽ የዘር በሽታ መድኃኒት አለው የማታ'ማታ ሀገር በወገን እንዴት ይረታ ፍቅር በነገር እንዴት ይፈታ ዘር ሳይለያየን ወይ ሃይማኖት ከጥንት በፍቅር የኖርንባት እናት ኢትዮጵያ ውዲት ውዲቷ በጎጆ አያልቅም ሙሽርነቷ እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም (እማማ እማማ) የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ የሦስት ሺህ ዓመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ እቴ አንቺ የኔ ሙሽራ ሀገሬ እስኪ ልጠይቅሽ ያገቡሻል ይፈቱሻል ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ ከክብርሽ በታች ወደቁ ነገሥታት በፍቅርሽ ተነድፈው ደናግላን መነኑልሽ ዓለምን ደስታቸውን ጥለው እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም (እማማ እማማ) የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ የሦስት ሺህ ዓመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ እቴ ማነው የሞሸረሽ አስጊጦ እንዲ ያሳመረሽ ያገቡሻል ይፈቱሻል ሀገሬ አሁንም ድንግል ነሽ ከክብርሽ በታች ወደቁ ነገሥታት በፍቅርሽ ተነድፈው ደናግላን መነኑልሽ ዓለምን ደስታቸውን ጥለው እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም (እማማ እማማ) ሀገር በውበት ወጥመድ ተይዛ የዘመን ስቃይ ጭንቅ እንደዋዛ እናት እራቁት እንዴት ልይሽ ክብርሽ የታለ አንድነትሽ አርበኛ አርበኛ አርበኛ አላይም ልውጣ መቅደላ ልበል ዋይ ዋይ ምነው ቢነሳ መይሳው ካሳ አልወድም ጎበዝ ጀግና ሲረሳ እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም (እማማ እማማ) (እማማ እማማ) (እማማ እማማ) እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም (ቃል የእምነት እዳ እንጂ ያ'ባት የ'ናት አይደለም) እማማ እናት ኢትዮጵያ እማማ አንቺ እናት ዓለም (ቃል የእምነት እዳ እንጂ ያ'ባት የ'ናት አይደለም)
Writer(s): Bill Laswell, Ejigayehu Shibabaw, Bill O Laswell Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out