Credits

PERFORMING ARTISTS
Abdu Kiar Kahssay
Abdu Kiar Kahssay
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Abdu Kiar Kahssay
Abdu Kiar Kahssay
Songwriter

Lyrics

አላምደሽ አላምደሽ ስትርቂኝ ተጎዳሁ ተዘባርቆብኛል አደባባይ ጓዳው ሰው አለ ሰው የለም ይመጣል ፈገግታሽ እልም ይላል ልቤ ርቆ በትዝታሽ እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ ይሄ ያላንቺ ኑሮ ሊያሳብደኝ ነው ዘንድሮ አቅም አሳጥቶኛል ከሰው ጋር መኖር ከብዶኛል ምነው ምነው እያሉ ጥያቄ ያበዙብኛል ባለፍኩበት ጎዳና ይጠቋቆሙብኛል እኔ በናፍቆት ብዛት ራሴን ጥዬልሻለሁ እሷስ ብቻዋን እዛ እንዴት ትሆን እላለሁ እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ እናፍጥነው እንተያይ እንጂ ህይወትማ ይከብዳል ያላንቺ ካንቺ ጋራ ስሆን ለጉድ የሚሮጠው ብቻዬን ሲያገኘኝ ጊዜን ምን ጎተተው አንድ ቀን እንዳመት እየረዘመብኝ አይንሽን ማይበት መምጫሽ ቀን ራቀብኝ እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ ልጠይቅሽ ልጠይቅሽ ውዴ ናፍቆት እንዲ ጤና ይነሳል እንዴ ይሄ ያላንቺ ኑሮ ሊያሳብደኝ ነው ዘንድሮ አቅም አሳጥቶኛል ከሰው ጋር መኖር ከብዶኛል ወፈፍ አድርጎ ያስቀበጣጥረኛል ብቻዬን አወራለሁ ምትሰሚኝ ይመስለኛል የኔ ጤና ተዛብቶ መስመር እያስለቀቀኝ ያንቺ ነገር ብቻ ነው ጧት ማታ የሚያስጨንቀኝ እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ እናፍጥነው እንተያይ እንጂ ህይወትማ ይከብዳል ያላንቺ እንደምነሽ እንደምነሽ ውዴ ካላየሁሽ አይቀርም ማበዴ ልጠይቅሽ ልጠይቅሽ ውዴ ናፍቆት እንዲ ጤና ይነሳል እንዴ እንደምነሽ እንደምነሽ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out