Credits
PERFORMING ARTISTS
Teddy Afro
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Teddy Afro
Songwriter
Lyrics
ይህቺ ሰንደቅ ዓላማ የክብር ምልክት
ሥፋት እና ምልዓት ርቀት አላት
በዓላማ አንድ ሆና ሦስት ናት በመልክ
ሆ
ላላ
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ብለን ተነስተናል ተስፋ አርገን ኹላችን
እኔ ለኔ ሳንል ቅድሚያ ለሀገራችን
እንደ ሐራሴቦን (ወጥተን ከሐራሴቦን) አንድ ዓላማ ይዘን
እንገባለን ከነዓን በፍቅር ተጉዘን
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
የጸና ነው በአንድነት ላይ መሠረታችን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ባንዲራችን
ማነው ደፍሮ በዘር ቋንቋ የሚነጣጥለን
እኛ እንደሆን እማንለያይ አንድ ነን
የጸና ነው በአንድነት ላይ መሠረታችን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ባንዲራችን
ማነው ደፍሮ በዘር ቋንቋ የሚነጣጥለን
እኛ እንደሆን እማንለያይ አንድ ነን
በዘር በሃይማኖት በማሰብ አንሰናል
ይብቃ በኛ ዘመን ታሪክ ይወቅሰናል
እንቁም ተያይዘን በአንድነት
በኢትዮጵያዊነት
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ዓላማ ነው አንድ ያረገን እኛን
አንድ ያረገን እኛን (፪)
ቤታችን ናት አትንኳት ኢትዮጵያን
አትንኳት ኢትዮጵያን (፪)
የአንድነት ኃይል ጨለማን ድል ነሥቶ
ጨለማን ድል ነሥቶ (፪)
እናያለን አዲስ ፀሐይ ወቶ
አዲስ ፀሐይ ወቶ (፪)
በዝምታ ብንመስልም የተኛን
ብንመስልም የተኛን (፪)
ከተነሣን ማን ሊያቆመን እኛን
ማን ሊያቆመን እኛን (፪)
ከሷ በፊት ይፈሳል ደማችን
ይፈሳል ደማችን (፪)
ቀልድ አናውቅም እኛ በሀገራችን
በእናት ሀገራችን (፪)
ዓላማ ነው
ዓላማ ነው አንድ ያረገን እኛን
አንድ ያረገን እኛን (፪)
ቤታችን ናት አትንኳት ኢትዮጵያን
አትንኳት ኢትዮጵያን (፪)
ከሷ በፊት ይፈሳል ደማችን
ይፈሳል ደማችን ()
አትምጡብን በቃ በሀገራችን
በእናት ሀገራችን
Writer(s): Teddy Afro
Lyrics powered by www.musixmatch.com