Top Songs By Theodros Kassahun
Similar Songs
Credits
COMPOSITION & LYRICS
Theodros Kassahun
Songwriter
Lyrics
ጡር ሰርተሽ በፍቅር: ገፍተሽ የኔን ገላ
ስጠይኝ ጠላሁሽ: ስትለምጂ ከሌላ
ማዘን መጨነቁን: መከፋቴን ትቼ
ከሰው ተላመድኩኝ: አንቺን ረስቼ
ጡር ሰርተሽ በፍቅር: ገፍተሽ የኔን ገላ
ስጠይኝ ጠላሁሽ: ስትለምጂ ከሌላ
ማዘን መጨነቁን: መከፋቴን ትቼ
ከሰው ተላመድኩኝ: አንቺን ረስቼ
እ-ህ
አንቺ እንደገፋሽኝ: እንዳወዳደቄ
ሰው አልሆንም ነበር: ባላሳልፍ ስቄ
ሰው አልሆንም ነበር: ባላሳልፍ ስቄ
ቢሰማሽም ፀፀት: መሽቱዋል ለይቅርታ
ሰው ገባ ከሆዴ: ላንች የለኝም ቦታ
ሰው ገባ ከሆዴ: ላንች የለኝም ቦታ
ጡር ሰርተሽ በፍቅር: ገፍተሽ የኔን ገላ
ስጠይኝ ጠላሁሽ: ስትለምጂ ከሌላ
ማዘን መጨነቁን: መከፋቴን ትቼ
ከሰው ተላመድኩኝ: አንቺን ረስቼ
በቃ በቃ ሸኘሁሽ
አንቺን በሰው ተካሁሽ
በቃ በቃ ሸኘሁሽ
አንቺን በሰው ተካሁሽ
አንቺን አጣሁ ብሎ: ሆዴን እማይብሰው
ይዋል ይደር እንጂ: ሰው ይተካል በሰው
ይዋል ይደር እንጂ: ሰው ይረሳል በሰው
መተኪያ የሌለው: ለናት ሞት ነው እንጂ
ወዳጅማ ቢሄድ: ይመጣል ወዳጅ
ወዳጅማ ቢሄድ: ይመጣል ወዳጅ
ጡር ሰርተሽ በፍቅር: ገፍተሽ የኔን ገላ
ስጠይኝ ጠላሁሽ: ስትለምጂ ከሌላ
ማዘን መጨነቁን: መከፋቴን ትቼ
ከሰው ተላመድኩኝ: አንቺን ረስቼ
እ-ህ
ዛሬስ እርም አወቀ: ያንተራሰሽ ክንዴ
ዳግመኛ ላይወድሽ: ጨከነብሽ ሆዴ
ዳግመኛ ላይወድሽ: ጨከነብሽ ሆዴ
ዛሬስ እርም አወቀ: ያንተራሰሽ ክንዴ
ዳግመኛ ላይወድሽ: ጨከነብሽ ሆዴ
ዳግመኛ ላይወድሽ: ጨከነብሽ ሆዴ
ጡር ሰርተሽ በፍቅር: ገፍተሽ የኔን ገላ
ስጠይኝ ጠላሁሽ: ስትለምጂ ከሌላ
ማዘን መጨነቁን: መከፋቴን ትቼ
ከሰው ተላመድኩኝ: አንቺን ረስቼ
በቃ በቃ ሸኘሁሽ
አንቺን በሰው ተካሁሽ
በቃ በቃ ሸኘሁሽ
አንቺን በሰው ተካሁሽ
በቃ በቃ ሸኘሁሽ
አንቺን በሰው ተካሁሽ
በቃ በቃ ሸኘሁሽ
አንቺን በሰው ተካሁሽ
Written by: Theodros Kassahun