Featured In

Top Songs By Alemayehu Getachew

Lyrics

በተትረፈረፈ ሞልቶ በፈሰሰ ላንቺና ለኑሮ እንዲያው ስም አነሰ በተሰጠሽ ጸጋ ከላይ ባገኘሽው ጨምረሽ ጨምረሽ ፍቅሬን አባባሽው አብሺው አብሺው አባብሺው በጭራሽ በጭራሽ አትቀንሺው መጨመር ነው እንጂ በየዕለቱ ልብ ለማይገዛው ለኔ አይነቱ ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ ስበሽ ካስገባሽኝ በኋላ ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ የምን ማፈግፈግ ነው ወደ ኋላ ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ ከገቡማ አንዴ ከሜዳው ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ ወደ ፊት ነው ከሐሳብ የሚነዳው ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ በዪማ በዪ (አብሺው) ያምራል ጭፈራ (አብሺው) ባንቺማ ላይ (አብሺው) በዪማ በይ... (አብሺው) ደርሰሽ ተቃጥለሽ (አብሺው) ዝም አትበዪኝ (አብሺው) የዕለቱ ገበያ ስሰማ እየናረ እሱን ሳብሰለስል ቀልቤ ርቆኝ ቀረ አሁን ግን ሲገባኝ የጥያቄው መልሱ ወዝ ወዝ ማለት ነው ካ'ሳብ ሲመለሱ አይደለም እንዴ አይደለም እንዴ ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ በሐሳብ ተገናኝተው ክንፍ ያሉ ዕለታ እንዴት ያስደስታል ከሀገር ልጅ ጨዋታ ወጋ ወጋ አድርጎ በቀላል በቀላል ከሚወዱት ጋር መጫወት ደስ ይላል አይደለም እንዴ አይደለም እንዴ ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ አርማሽ ነፃነት ነው ምድርሽ አረንጓዴ ድማም የሀገሬ ልጅ አይደለሽም እንዴ ውበት ደም ግባትሽ በሀገር ልብስሽ ፈክቶ አስቸገረኝ እንጂ ጥርጣሬሽ በዝቶ አይደለም እንዴ አይደለም እንዴ ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ ማናት አትበይኝ ስልኬ ሲጮኽ ድንገት ሐናም ጎረቤቴ ሣራም እኅቴ ናት እንደ ራስሽ እዪው ግድ የለም አንዳንዴ የአጎቴ ልጅ ስትዪ አምንሽ የለም እንዴ አይደለም እንዴ አይደለም እንዴ ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ እንዲህ ነው አንዳንዴ! ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ ስበሽ ካስገባሽኝ በኋላ ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ በኔ እንዳታሳብቢ በኋላ ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ ወደ ፊት ነው እንጂ በርትቶ ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ ታሞ እንጂ አይሞትም ሰው ፈርቶ ወደ ኋላ የለም ወደ ኋላ በዪማ በዪ (አብሺው) ይለኛል ዛሬ (አብሺው) የኔስ ጉዳይ (አብሺው) በዪማ በይ... (አብሺው) ደርሰሽ ነካክተሽ (አብሺው) ዝም አትበዪ (አብሺው) መዝነን ካየነው ሁሉንም በፍቅር ከሐዘን ሳቅ ይወጣል ከቀልድም ቁም ነገር መጫወት ነው እንጂ ፍቅር ይዞ ብልጫ የፀባይ ነው እንጂ ለፀብ የለው ዋንጫ አይደለም እንዴ አይደለም እንዴ ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ ካዋልሺኝ ጋር ሳልውል ካሰብሺኝ ሳላድር ምን ይሉታል ያንቺን ደርሶ መጠራጠር ችሎታ ሳያንስሽ ባመል በፀባይ በገዛ ሜዳሽ ላይ ነጥብ አትጣይ አይደለም እንዴ አይደለም እንዴ ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ ገሃድ ወጣ ብለሽ የቤቴ ገመና ቂም አትይዢም በኔ የገባሽ ነሽና ካጠፋውም ይኸው ማሪኝ በይ በሰው ፊት ትርፉ መዓቀብ ነው ካንቺ ጋር መጣላት አይደለም እንዴ? አይደለም እንዴ? ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ ያፀናነን ፍቅር ያቆየንን አይቶ ማየት የተመኘ ከሐሳብ ጭንቀት ወቶ እንደኛ በፍቅር እንዲያብብ በሕይወቱ ሁሉም ይሞክረው ገብቶ በየቤቱ አይደለም እንዴ? አይደለም እንዴ? ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ? አይደለም እንዴ? አይደለም እንዴ? ዋሸው እንዴ? አይደለም እንዴ? እንዲህ ነው አንዳንዴ!
Writer(s): Alemayehu Getachew Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out