Lyrics

የኔ ብቸኛ የትም ዞሬ ስደርስ ደጃፍ ግርጌ እጣራለሁ ስምሽን ከፍ አድርጌ ካለሽ መልካም ከሌለሽ ነው ጉዱ በድን ቤትን ይከብዳል መልመዱ አንቺ ሁሌ እኔኑ ጠባቂ ቀን ይበራል አይተሽኝ ስትስቂ ያኔ ሁሉም ለኔ ይስተካከላል መኖርሽ ብቻ ያኖረኛል ነብሴን ይዤ እንዳልሰጥሽ አልተቻለኝም ላንድያ ልጅሽ ፈጣሪ ይርዳኝ ዘመኔን እንዳይሽ ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ በእውቀት ቀለም ብሆን የመጠኩኝ በስልጣኔ ሀገር ያስጨነኩኝ ይሄ ሁሉ አንቺን መች ሊገርምሽ ሁሌም ልጅ ነኝ እኔ ላንቺ ልጅሽ በመንገዴ ፀሎትሽ ይቀድማል ስንቱን ችግር ይዞ ያሻግረኛል ምንም ብሆን ነብስያሽ ይነግረኛል ስለኔ ብለሽ ስንቱ ውስጥ ገብተሻል ነብሴን ይዤ እንዳልሰጥሽ አልተቻለኝም ላንድያ ልጅሽ ፈጣሪ ይርዳኝ ዘመኔን እንዳይሽ ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ ነብስን በሚገርፈው በሀሩር በብርዱ ጠብ የሚል ባይገኝ ባይቀናም መንገዱ አንቺ ግን ስለኔ ሁሉንም ቧጠሻል ፍቅርሽ ወሰን የለው ምንስ ያግድሻል ልጄ ልጄ እያልሽ ስላንቺ ሳትኖሪ ቤቱ እንዳይጓደል ቀልጠሽ የምትበሪ ውለታሽ ቢበዛ አንድ ሆነ ፀሎቴ አንቺን ያቆይልኝ ያኑርሽ እናቴ እማማ ኡ እናትዬ ማማዬ... ኡ እናትዬ... ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ
Writer(s): Sami Dan Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out