Lyrics

አንጀራውን ይስጥህ በውል እያሰፋ መልካም ሰው ነህ እና ብትበላ አይከፋ እንዴት ነው ሞንሟንዬ እህም እናኑ እህም እናኑ እህም እናኑ እህም እናኑ እህም እናኑ እህም እናኑ እናናን እናናን እናና ይጥለፈኝ ቀሚሷ ጉብኗ ጠብ እርግፍ ያድርገኝ ለክብሯ ሆዴ እንዳታጣላኝ ከአድባሯ እናናንየ እናት ዓለም የደሜ አለላ ሰበዝ ቀለም እናናንየ እናት ዓለም የደሜ አለላ ሰበዝ ቀለም ኧረረረ ኧረ ሰው ኧረ ሰው ኧረ ሰው ጌጥ ሀብቱ ኧረ ሰው ኧረ ሰው ኧረ ሰው ኧረ ሰው ኩራቱ እንደምን አይከፋው አንገቱን አይደፋው ሲከፋት እናቱ ኧረረረ በልጅነት ፍቅርሽ የሰቀልኩት ሰንደቅ የታቀፍኩት በእጄ የዜግነት ክብር ስል የዘመርኩበት ከሰልፋ ማልጄ ያቆመኝ አድባርሽ የነፃነት ደጄ እሱ ነው እሱ ነው እሱ ነው ወዳጄ ከአንኮላሽ ብርዝ ውሀ ማርና ወተት ማርና ወተት ከእጅሽ ቆሎ አፍሼ በቀሚሴ ጫፍ ላይ የቋጠርኩበት ቢጠማኝ ቅራሪ ቢርበኝ እሸት ቢርበኝ እሸት ሳድር ቀማምሼ ፍቅር ተዋውሼ ያሳለፍኩበት ኧረ ጎራው ኧረ ዱሩ ጃል እንዴት ነው ዳር ድንበሩ የሷን ክፋ ቆሜ ከማይ ያሳደገኝ አፈር ይብላኝ ኧረ ጎራው ኧረ ዱሩ ኧረ ጎራው ኧረ ዱሩ አረገኝ አረገኝ ንቢቷን ቀፎዋን የነካኩት ቤቷን አረገኝ አረገኝ ፍም እሳት ሰማይ ሀገሬን ሲንቃት ባይ ከአንገት በላይ በላይ ሁሉ ከአንገት በላይ በላይ ያለ ሀገር ኑሮ ስቃይ ማን ኢትዮጵያን መሳይ ሲሳይ ሲሳይ ነች እሷ ሲሳይ ኧረ እናናዬ ኧረ እናና እናናንዬ እናና እናናይ ኧረ እናዬ እናናዬ (እህም እናኑ ፣ እህም እናኑ ፣ እህም እናኑ ፣ እህም እናኑ ፣ እህም እናኑ) አንጀተ ስፍስፋ ያወገኔ ደሀው ያገኔ ደሀው መቻሉ ሳያንሰው ሲመር እሀል ውሀው ሲመር እህል ውሀው አትንኩት አትንኩት አልያ አታስከፉት ይነሳኛል ጤና አፈር ከፍቶ ለፍቶ ያጎራረሰኝን አልረሳውምና ሆ በል ሲሉት ክተት ጀማው እየራበው እየጠማው ህይወት ደሙን ለሚሰጠኝ ብሞትለት ሞት አነሰኝ አረ ጎራው አረ ዱሩ አረ ጎራው አረ ዱሩ አረገኝ አረገኝ ንቢቷን ቀፎዋን የነካኩት ቤቷን አረገኝ አረገኝ ነበልባል በአባይ ሰንደቋ እንዲያ ሲጣል ባይ ከአንገት በላይ በላይ ሁሉ ከአንገት በላይ በላይ ያለ ሀገር ኑሮ ስቃይ ማን ኢትዮጵያን መሳይ ሲሳይ ሲሳይ ነች እሷ ሲሳይ ኧረ እናናዬ ኧረ እናና እናናንዬ እናና እናናይ ኧረ እናዬ እናናዬ (እህም እናኑ ፣ እህም እናኑ ፣ እህም እናኑ ፣ እህም እናኑ ፣ እህም እናኑ)
Writer(s): Samuel Alemu, Rahel Getu Unknown Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out