Music Video

Teddy yo New Album 2018 Arada Relesed Songs
Watch Teddy yo New Album 2018 Arada Relesed Songs on YouTube

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Teddy Yo
Teddy Yo
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Solomon Ambaw
Solomon Ambaw
Songwriter

Lyrics

አ እሺ ልጅ እያሱ jungle productions ችግር ችግርን ሲወልድ ጭንቀቱ ሲደራረብ ረሀብ ሲጠናብኝ ተተብትቤ በሱስ መረብ የልጅነት ህልሜ እንደጉም ሲበታተንተን አለሁ በለኝ ጌታዬ እኔን አለሁ በለኝ ወገን ፊቷን ስታዞርብኝ ያደኩባት መሬት የአብሮ አደግ ተመፅዋች መሆን ይመራል እንደ ሬት የማይቻል የለም ይሄንንም ልቻል መቼስ ዘመድ የለኝ የሚመለከተኝ እኔን ዞሮ ታላቅ እህቴ ቡና ቤት ወንድሜ ሊስትሮ ሲርበኝ አድራለሁ ቆርጥሜ የ አስር ሳንቲም ቆሎ ጌታ ካላለፈልኝ ውሰደኝ አሁን ቶሎ የትኛው ሰው ጆሮ ሰቶ ሰማ የኔን ሮሮ የጪስ መአት ሲጎርፍበት ከደረቀው ጉሮሮ እህ ዘላለም ተማሮ ህይወት መተንፈስ ሆነና ይህም ተባለ ኑሮ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ ፀሀይ ጉልበት ሲከዳት ደመና ፊቱን ሲያጨልም መጣሁ ቀረሁ እያለ ዝናብ ድምፁን ሲያስገመግም ሆዴን በባዶ ይዤ ወደ ጎዳና ቤቴ ሳዘግም አንተ አለሁ በለኝ አንተ አለሁ በለኝ ፀሀይ ጉልበት ሲከዳት ደመና ፊቱን ሲያጨልም መጣሁ ቀረሁ እያለ ዝናብ ድምፁን ሲያስገመግም ሆዴን በባዶ ይዤ ወደ ጎዳና ቤቴ ሳዘግም አንተ አለሁ በለኝ አንተ አለሁ በለኝ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ ጎህ ሲቀድ በማደሬ ስረጋጋ የያዝኩትን ነጥቆ በላ ከመንጋጋ በየምግብ ቤቱ ስዞር ሚቀመስ ፍለጋ ስገረፍ ውላለሁ በረሀብ አለንጋ ጡቷ ደርቆባት እናት ሲንሰቀሰቅ ልጇ ሁሉን ስትማፀን ዛሬ ተዘርግቶ እጇ በሀዘን ስታነባ ሁሌ ጠፋና ወዳጇ ጌታ አየዋለሁ በለኝ በጭንቅ ባማላጇ በሚቆረጥም ብርድ ላይ በጎዳና ብወለድም አጥቼ እንጂ የሚሰማኝ ብዬ ነበር አልወለድም ቅንጦት ያሰቃየው ቢበዛባት በዚች አለም ለቀበጠቺው ሁሌ ያድራል ደሞ ሲሸላለም ልመናን አልፈልግም የሰው ኪስን ቧጦ ፍላጎቴ መለወጥ ነው ሰርቶ ማደግ ሮጦ ማየት እፈልጋለሁ ህይወት ተለውጦ አሁን ምኖረው ኑሮ ታሪክ ተገልብጦ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ ፀሀይ ጉልበት ሲከዳት ደመና ፊቱን ሲያጨልም መጣሁ ቀረሁ እያለ ዝናብ ድምፁን ሲያስገመግም ሆዴን በባዶ ይዤ ወደ ጎዳና ቤቴ ሳዘግም አንተ አለሁ በለኝ አንተ አለሁ በለኝ ፀሀይ ጉልበት ሲከዳት ደመና ፊቱን ሲያጨልም መጣሁ ቀረሁ እያለ ዝናብ ድምፁን ሲያስገመግም ሆዴን በባዶ ይዤ ወደ ጎዳና ቤቴ ሳዘግም አንተ አለሁ በለኝ አንተ አለሁ በለኝ ዝናብ ቤቴን ሲያፈርሰዉ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ለማን እከሰዋለው ማን አዛዥ የለው እሱማ ነገን ማሰብ አቁሚያለሁ ተስፋዬ ደብዝዞ የኔ መከራ እንደው አያልቅ እንደዋዛ ተመዞ መቼ ነው እንደሰው ምኖር እንደወፍ መኖር ትቼ የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገንም አስልቼ አለሁ በለኝ አይሁንብኝ ጌታዬን መፈታተን የጎዳና ልጆችህን በቅዱስ እጅህ ባርከን አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ አለሁ በለኝ ጌታዬ በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ አለሁ በለኝ በቃ በለኝ አንተ አለሁ በለኝ አንተ አለሁ በለኝ አንተ አለሁ በለኝ አንተ አለሁ በለኝ
Writer(s): Solomon Ambaw Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out