Lyrics

ነፍሴ ሆይ(፫)እግዚአብሔርን ባርኪ አጥንቶቼም(፫)ሁሉ የተቀደሰ ስሙን በደስታ ዘምሪ በአዲስ ምስጋና ጸጥታና ሰላም አድሎሻልና መሰንቆውን አንሺ ቅኔ ተቀኚለት ለውጦሻልና በደስታ ዘይት አዝ ሐሴትን አድርጊ ነፍሴ በእግዚአብሔር ይሰጥሻልና በክብር ላይ ክብር ደሴቶች ሲያነቡ በደስታ መንፈስ እየተወያዩ ስለ ሥሉስ ቅዱስ አዝ ሰማያት ሲያወሩ ጽድቅን ሲወያዩ ሲጠራው አድምጪ ቀላዩን ቀላዩ ደመናው ጭጋጉ በዙሪያው ከበውት ቅኔ ያቀርባሉ ለፍጥረታት አባት አዝ መብረቅም ይሰማል ሰማዩን ሰንጥቆ ምስጋናውን ሊያቀርብ ግዜውን ጠብቆ ከፊቱ ይነዳል እሳትም በግርማ ምድር ተናወጠች ነጎድጓዱን ሰምታ
Writer(s): Simone Tsegay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out